Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለአንድ ዓመት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በደቡብ ሱዳን ያለውን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም ድምጽ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
ምክርቤቱ ሀገሪቱ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳትመለስ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግም ጥሪ አቅርቧል።
በዩናይትድ ስቴትስ የተደገፈው ይህ የውሳኔ ሃሳብ÷ በምክር ቤቱ 13 ድምጽ ሲያገኝ ቻይና እና ሩሲያ ድምፀ-ተዓቅቦ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
የሰላም ማስከበር ተልኮው በመራዘሙ በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ የተሰኘው የሰላም አስከባሪ ሃይል አስከ ፈረንጆቹ መጋቢት 15 ቀን 2023 ድረስ በደቡብ ሱዳን ቆይታ እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡
የሰላም አስከባሪ ሰራዊቱ በ17ሺህ ወታደሮች እና በ2 ሺህ 101 ፖሊሶች የተዋቀረ እንደሆነ መገለጹን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
አሁን ላይ የተመድ 17 ሺህ ወታደሮች እና 2 ሺህ 101 ፖሊሶች ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ በደቡብ ሱዳን መሰማራታቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.