የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ ገደብ ተነሳ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮቴሌኮም ቴሌብርን በመጠቀም የሚደረገውን ዕለታዊና ወርሃዊ የገንዘብ እንቅስቃሴ ገደብ ማንሳቱን አሰታወቀ።
ከዚህ በፊት ተጥሎ የነበረው ዕለታዊ እና ወርሃዊ የገንዘብ እንቅስቃሴ ገደብ በመነሳቱ ደንበኞች ግብይትን ያለገደብ መፈጸምና ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚቻሉ ገልጸዋል።
ደንበኞች በቴሌብር ዕለታዊ የገንዘብ እንቅስቃሴ 5ሺህ ብር፣ ወርሃዊ የገንዘብ እንቅስቃሴ 30 ሺህ ብር ገደብ የነበረው ሲሆን÷ አሁን ላይ ያለገደብ የፈለጉትን ያህል ገንዘብ ማስተላለፍና ግብይት መፈጸም እንደሚችሉ ኢትዮቴሌኮም በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
የቴሌብር አገልግሎት ለማህበረሰቡ ምቹና ሁሉን አካታች የገንዘብ ማስተላለፊያና የመገበያያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ሲሆን÷ደንበኞች የስልክ ቁጥራቸውን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ መላክ፣ ግብይት መፈጸም፣ ገንዘብ ማጠራቀምና መቀበል የሚያስችል መሆኑን ይታወቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!