Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ያካሄደው 10ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት÷ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
የመስተዳድሩ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፥ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የሚከናወኑ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ወጪያቸውን መሸፈን ላልቻሉ ወረዳዎች የበጀት ድጎማን በሚመለከት፣ ለልማት ተነሽ ለሚሆኑ ባለመሬቶች የሚከፈል ባህር ዛፍ ካሳ ክፍያ፣ የርዕሳነ መምህራን፣ ምክትል ርዕሳነ መምህራንና ሱፐር ቫይዘሮች ምልመላና መረጣ እንዲሁም የስራ ስምሪትና የደረጃ ዕድገት በሚመለከት በቀረቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ምክር ቤቱ በጥልቀት ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል።
በክልሉ በሚከናወኑ ወቅታዊ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውንም ገልጸዋል።
የክልሉን ሰላምና ልማት በሚያረጋግጡ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይም የመስተዳድሩ ምክር ቤት የጋራ አቋም ላይ መድረሱን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.