አብን ዶክተር በለጠ ሞላን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶክተር በለጠ ሞላን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
አቶ መልካሙ ሹምዬ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
አብን ለሦስት ቀናት ሲያካሂድ በቆየው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው የሥራ አስፈፃሚ አባላቱን በአዲስ በማደራጀት ማጠናቀቁን የፖርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጣሂር መሐመድ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት፦
ዶክተር በለጠ ሞላ – ሊቀመንበር
መልካሙ ሹምዬ – ምክትል ሊቀመንበር
ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ – የውጭ ግንኙነት ኃላፊ
ዩሱፍ ኢብራሒም – የሕግ ጉዳዮች ኃላፊ
ክርስቲያን ታደለ – የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ክፍል ኃላፊ
ጋሻው መርሻ – የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ
ጣሂር መሐመድ – የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ዶክተር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም – የአብን ጽህፈት ቤት ኃላፊ
ሐሳቡ ተስፋየ – አደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ አድርጎ የሥራ አስፈፃሚውን በአዲስ አደራጅቷል።
ከተመረጡት የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚዎች መካከል 3ቱ አዲስ መሆናቸው ተገልጿል።
ፖርቲው በዛሬው ዕለትም 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በባህር ዳር ማካሄድ ጀምሯል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!