Fana: At a Speed of Life!

የቱሪዝም ሚኒስቴር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር በቅንጅት ለመስራት ምክክር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር በቅንጅት ለመስራት ምክክር ማካሄዱን ገለጸ፡፡
በቱሪዝም ሚኒስትሩ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የተመራ ልዑክ ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በማምራት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ነጋሽ ዋጌሾ እና ከክልሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስህብ ሃብቶችን በማልማት፣ በማስተዋወቅ፣ የማሕበረሰቡን ተጠቃሚነት እና የክልሉን ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ሁኔታዎቸ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የገበታ ለሃገር ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ በሚመለከት ውይይት መካሄዱ ተገልጿል።
በቱሪዝም ሃብት ልየታ እና ምዝገባ፣ ለገበታ ለሃገር ፕሮቶች በሚደረግ ድጋፍ፣ በመዳረሻና ምርት ልማት ስራዎች፣ በቱሪዝም ገበያ ልማትና ፕሮሞሽን ስራዎች፣ በቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ብቃት ማረጋገጥ፣ እውቅና አሰጣጥ እንዲሁም ደረጃ ምደባ ላይ በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ሚኒስትሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም በቁጥጥር እና ድጋፍ ስራዎች፣ በእቅድ፣ ሪፖርትና የስራ አፈፃፀም ግምገማ ስርዓት፣ በቱሪዝም መረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓት፣ በሰው ሃይል አቅም ግንባታ ስራዎች እና በመሳሰሉት መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን÷ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና አመራሮችም በትብብር እና ለቱሪዝም ልዩ ትኩረት ሰጥተው ለመስራት ስምምነታቸውን ገልፀዋል።
ክልሉ አዲስ እንደምሆኑ መጠን የቱሪዝም ቢሮውን በማደራጅት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተናግረዋል።
ከውይይቱ ጎን ለጎን ልዑኩ በአካባቢው የሚገኙ የገበታ ለሃገር ፕሮጀክቶችን ጨምሮ፣ የኮይሻ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን፣ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክን እና ሌሎች የአካባቢውን የቱሪዝም መስህብ ሃብቶችን እና እየተሰሩ ያሉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን መጎብኘታቸውን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.