ለአራተኛው ዓመት አረንጓዴ ዐሻራ ቅድመ ዝግጅቶች እየተካሄዱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፁ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአራተኛው ዓመት አረንጓዴ ዐሻራ ቅድመ ዝግጅቶች እየተካሄዱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡
በመጪው ክረምት የአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ አራተኛ ዓመቱን እንደሚይዝ ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፥ ለአራቱ ዓመት ያቀድነውን ግብ ለማሳካት ብቻ ሳይሆን፣ ታሪክ የሚቀይር ውጤት ለማስገኘት ችግኝ የማፍላት ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ ነው ሲሉ ማስፈራቸው ይታወሳል።
ክረምት ሳይገባም ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የዝናብ ውኃ ለማቆር እና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት እጅግ ተስፋ ሰጪ መሆኑንም አመላክተው ነበር፡፡
ከመጪው የዝናብ ወቅት አስቀድሞም በመላ ኢትዮጵያ በቂ ዝግጅት እንዲደረግም ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!