Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን መሪዎች ለዩክሬን የሚያደርጉትን የተለያዩ ድጋፎች ለማጠናከርና ለማስፋፋት ተስማምተዋል፡፡

የምዕራባውያን የቡድን 7 ሀገራት መሪዎች በብራሰልስ ባካሄዱት ስብሰባ፥ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረገችውን ወረራ እንደሚያወግዙ እና ለዩክሬን ወታደራዊና ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና ጸሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ኔቶ ወታደሮቹን በዩክሬን ምድር እንደማያሰማራና ከሩሲያ ወታደሮች ጋር በቀጥታ ግጭት ውስጥ እንደማይገባ ዳግም አስታውቋል፡፡

ዋና ጸሃፊው አክለውም ፥ ለግጭቱ የምንሰጠው ምላሽ የዩክሬንን መንግስት በማስታጠቅ ነው ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።

በውይይቱ ኔቶ በዩክሬን አቅራቢያ በሚገኙ ወታደራዊ ሃይል የሚመደብባቸውን አራት የምሥራቅ አውሮፓ ሀገራት ይፋ ያደረገ ሲሆን ፥ ለወታደራዊ እቅዶቹ መሳካት አሜሪካ እና እንግሊዝ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡

ተጨማሪ የኔቶ ወታደራዊ ኃይሎችን ወደ ቡልጋሪያ፣ ሀንጋሪ፣ ሩማንያ እና ስሎቫኪያ ለማሰማራት መወሰኑንም ነው ዋና ጸሃፊው ያመለከቱት።

ኔቶ ቀደም ሲልም በኢስቶንያ፥ ላቲቪያ፣ ሉቲንያ እና ፖላንድ ውስጥ የጦር ሰፈር እንዳለው ይታወቃል።

የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ እንደማይገባ በድጋሜ ያረጋገጠ ቢሆንም፥ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች ተጠናክረው እንደሚጥሉና ከአሁን በፊት የተጣሉት ማዕቀቦችም እንዲራዘሙ ወስኗል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.