ምዕራባውያን በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ሚዛናዊነት ይጎድላቸዋል – ቻይና
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን ሰብአዊ መብትን በተመለከተ የሚያሳዩት ሚዛናዊነት የጎደለው አተያይ ተቀባይነት እንደሌለው ቻይና ገለጸች፡፡
ቤጂንግ ምዕራባውያን ሀገራት በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታን እና በሶሪያ በነበረው ጦርነት እና ሰብአዊ መብት ላይ እና አሁን እየተካሄደ ባለው የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ላይ እያሳዩት ያለው አቋም ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ብላ እንደምታምን በሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን በኩል ገልጻለች።
ቃል አቀባዩ እንዳሉት ምዕራባውያን ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ከአፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ የሚሰደዱ ስደተኞችን ችላ በማለት ሙሉ ትኩረታቸውን በዩክሬን ስደተኞች ላይ ማድረጋቸው ትዝብት ላይ ይጥላል፡፡
በዩጎዝላቪያ፣ አፍጋኒስታን፣ ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ በንጹሀን ላይ የሚደርሰውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ወደጎን በመተው በዩክሬን ንጹሀን የሚደርሱ ጥቃቶችን የጦር ወንጀል ናቸው ብሎ መጥራት ተቀባይነት የሌለውና ሚዛናዊነት የጎደለው ድርጊት ነው ብለዋል።
የሁሉም ሀገራት ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት አምናለሁ ያሉት ቃል አቀባዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር፣ ዓላማዎች እና መርሆዎች ግን መከበር አለባቸው ማለታቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!