Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለወዳጅ አገራት የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛል- ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለወዳጅ አገራት የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡
በታንዛኒያ መከላከያ ኃይል የዘመቻና ስልጠና ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ጃኮብ ጆሃን ማኩንዳ የተመራው ልዑካን ቡድን አባላት በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳየታንዛኒያውን መከላከያ ኃይል የዘመቻና ስልጠና ዋና አዛዥ በቢሯቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት እንደገለፁት÷ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳለው ሁሉ ከታንዛኒያ ጋርም በላቀ ትብብር ለመስራት ዝግጁ ነው።
ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ በአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ሳይንስ፣ በበረራና ጥገና፣ በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የሰው ኃይል አቅምን በማሳደግ ከአፍሪካ ጠንካራ የአየር ኃይል ግንባታ ራዕዩን በፍጥነት እያሳካነው።” ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በሚያስችል ቁመና ላይ ይገኛል ያሉት ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ የታንዛኒያን አየር ኃይል በሁሉም ረገድ ለማገዝ ቁርጠኛ አቋም አለን ብለዋል።
በታንዛኒያ መከላከያ ኃይል የዘመቻና ስልጠና ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ጃኮብ ጆሃን ማኩንዳ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ጀምሮ በአቪዬሽን፣ በአየር መካላከያውና በሰው ኃይል አቅሙ በምሳሌነት የሚጠቀስ ትልቅ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።
የታንዛኒያ አየር ኃይል ከአፍሪካ ቀደምት ታሪክ ካለው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጋር በቅርበት ለመስራት እቅድ እንዳለው የጠቆሙት ሜጀር ጀነራል ጃኮብ ጆሃን ማኩንዳ÷ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና መስተንግዶ በልዑካን ቡድኑ ስም ማመስገናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.