Fana: At a Speed of Life!

በመጅሊስ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ የተደረገው ውይይት በስኬት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጅሊስ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ የተደረገው ውይይት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ በስኬት መጠናቀቁ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።
በመጅሊሱ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የቆየውን ውይይት በማስመልከት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ መግለጫ ሰጥተዋል።
በውይይቱ 23 ዑለማዎች መሳተፋቸውን ጠቅሰው በጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር በማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
በውይይቱም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን÷ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የክልል ዑለማ ተወካዮችና ከመጅሊስ ውጪ ያሉ ዑለማዎች እንዲወያዩበት ይደረጋል ብለዋል።
የዳዒ ተወካዮች፣ ወጣቶችና ሴቶች ጭምር በውይይቱ እንዲሳተፉ የሚደረግ መሆኑንም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።
ከረመዳን ፆም በኋላ ውይይቱ እንዲካሄድ ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቅሰው ከውይይቱ ቀጥሎ አስመራጭ ኮሚቴ በማቋቋም የመጅሊስ አባላት ምርጫ ይካሄዳል ብለዋል።
በዚህም ለአንድነትና ለሰላም የሚሰሩ ተወካዮች መጅሊሳቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲረከቡ ይደረጋል ነው ያሉት።
ሰላምና አንድነት ለሁላችንም ይበጃል ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ÷ ህዝበ ሙስሊሙ በመካከላችን ልዩነት አለመኖሩን ሊያውቀው ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ታላቁን የረመዳን ፆም በፍቅር፣ በእዝነት እና አብሮነት በመፆም ለማሳለፍ ሁላችንም ልንዘጋጅ ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.