Fana: At a Speed of Life!

ከ90 በላይ ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር መስጠማቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ90 በላይ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በሜዲትራንያን ባህር መስጠሟ ተሰማ።
ጀልባዋ በሳምንቱ መጨረሻ ከሊቢያ ስደተኞችን ጭና ወደ አውሮፓ ለማሻገር ስትሞክር መስጠሟን አሶሺየትድ ፕረስን ጠቅሶ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
አፍሪካውያን ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊቢያን እንደ መነሻ ይጠቀማሉ።
ይሁን እንጅ በዚህ ጉዞ በርካቶች የባህር ሲሳይ ሆነው እንደሚቀሩ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ከፈረንጆቹ ጥር 1 እስከ መጋቢት 28 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ 300 የሚጠጉ ስደተኞች በማዕከላዊ ሜዲትራንያን ባህር ሰጥመው ህይወታቸው እንዳለፈ የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት አስታውቋል፡፡
ባለፈው አመትም 1 ሺህ 553 ስደተኞች በዚህ ጉዞ ለህልፈት መዳረጋቸውን ድርጅቱ አስታውሷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.