ዩ ኤስ ኤይድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሶስት ሀገራት የ114 ሚሊየን ዶላር እርዳታ አደረገ
አዲስ አበባ፣መጋቢት 29፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) በአፍሪካ ቀንድ ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ 114 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ድጋፉ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ እንደሚውል የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል።
በቀጠናው ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ 20 ሚሊየን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሎ ይታመናል።
የተረጅዎች ቁጥር ከ2016-2017 ከነበረው 70 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ነው የተገለጸው።
እርዳታው በቂ አለመሆኑን የገለፀው ድርጅቱ፥ ሌሎች ዓለም አቀፍ ለጋሽ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል።