የአፍሪካ አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 400 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር አጥተዋል
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 400 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ማጣታቸውን ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (አያታ) አስታወቀ።
የገቢ ቅናሹ ቫይረሱ በቻይና ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የተመዘገበ መሆኑም ተገልጿል።
የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ራፋኤል ኩቺ እንዳሉት፥ አየር መንገዶቹ ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ በማቋረጣቸውና በመሰረዛቸው ምክንያት የሚያገኙት ገቢ ቀንሷል።
የቫይረሱ ስርጭት በአፍሪካ ሃገራት አየር መንገዶች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ የከፋ እንደሚሆንም ገልጸዋል።
የደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ግብጽ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ሞሪሺየስ አየር መንገዶች ወደ ቻይና በረራ ማቋረጣቸው ይታወሳል።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል።
አሁን ላይ ሃገራት ቫይረሱን ለመከላከል የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ሲሆን፥ ቫይረሱ የዓለም ጤና ድርጅትም ጠንካራ የጤና ስርአት የሌላቸው ሃገራት ላይ ከፍ ያለ ጉዳት እንደሚያደርስ አስጠንቅቋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision