Fana: At a Speed of Life!

ለአብርሆት የመጽሐፍት ማሰባሰቢያ የሙዚቃና የኪነ ጥበብ ዝግጅት ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአብርሆት ቤተ መጽሐፍት አላማውን መጽሐፍት ማሰባሰብ ያደረገ የሙዚቃና ኪነ ጥበብ ዝግጅት ሊካሄድ ነው።
የአብሮሆት ቤተ መጽሐፍት ኃላፊ አቶ መስፍን ገዛኸኝ ለዚህ መርሃ ግብር ስኬት የሙዚቃና የኪነ ጥበብ ዝግጅት ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በግራዝማች ኢንተርቴይመንት አስተባባሪነት በሚካሄደው በዚህ መርሃ ግብር ለቤተ መጽሐፍቱ የሚያስፈልጉት 4 ሚሊየን መጽሐፍት ለማግኘት ትልቅ እድል መሆኑን ተናግረዋል።
የሙዚቃና ኪነ-ጥበብ ዝግጅቱን ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለማካሄድ መታሰቡን የግራዝማች ኢንተርቴይመንት ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ግርማ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በዚህ የሙዚቃና ኪነ ጥበብ ዝግጅት 20 ሺህ መጽሐፍት ለማሰባሰብ መታቀዱን ጠቅሰው፥ የመግቢያ ዋጋው ለአንድ ሰው ሁለት መጽሐፍት መሆኑን ገልጸዋል።
በእለቱም ከመጽሐፍት ማሰባሰቡ ጎን ለጎን ለብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ከበጎ ፈቃደኞች ደም ለማሰባሰብ ታቅዷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.