በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ በታንዛኒያ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 20 ኢትዮያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
በዛሬው ዕለትም በመጀመሪያው ዙር÷ ዕድሜያቸው ከ11 እስከ 17 የሚሆኑ 20 ኢትዮያውያን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዚያ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርገዋል፡፡
በቀጣይ ሌሎች ዜጎችም ከእስር ተፈትተው ወደ አገር መመለስ በሚችሉበት ሁኔታ በመንግስት በኩል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!