Fana: At a Speed of Life!

በጉራጌ ዞን መንገድ ስቶ ወደ መኖሪያ ቤት የገባ ተሽከርካሪ የ2 ሕጻናትን ህይወት ቀጠፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ አዶሼና አቱርቸ ቀበሌ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መንገድ ስቶ ወደ መኖሪያ ቤት በመግባቱ የሁለት ሕጻናት ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የቸሀ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሙ እንደገለፁት፥ ትናንት ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ በመውጣት ወደ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ገብቶ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
መኪናው ከቤት ውስጥ የነበሩ ሦስት ሕጻናት ላይ በመውጣቱ የ8 ዓመት ሴት ልጅና የ4 ዓመት ወንድ ልጅ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸው ሲያልፍ÷ አንዱ ሕጻን በወልቂጤ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
መኖሪያ ቤቱም ከነ ንብረቱ መውደሙ ን እና አሽከርካሪው ግለሰብ ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ እንደሚገኙም ከጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.