Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ከ1 ሚሊየን ዶዝ በላይ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በ3ኛው የክትባት ዘመቻ እንደሚሰጥ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል 1 ሚሊየን 128 ሺህ 330 ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በሦስተኛው የክትባት ዘመቻ እንደሚሰጥ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሰላማዊት መንገሻ÷ የሦስተኛው ዙር ዘመቻ ውጤታማ እንዲሆን የተለያዩ ተግባራት መሰራታቸውን ጠቁመው÷ በዚህም የህብረተሰቡ የመከተብ ፍላጎት መጨመሩን ተናግረዋል።
ከጀተመረ ቀናትን ያስቆጠረው ሦስተኛው ዙር የክትባት ዘመቻ በህብረተሰቡ ዘንድ ክትባቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ አመራሮች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ያሳዩት አርዓያነት ከፍተኛ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በበኩላቸው÷ ከ4 ሚሊየን 569 ሺህ 339 ሰዎች መካከል 2 ሚሊየን 421 ሺህ 750 ያህሉ ከ12 ዓመት በላይ የሆኑና ለኮቪድ 19 ክትባት የተለዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከእነዚህ ውስጥም ክትባታቸውን አጠናቀው የወሰዱ ት ከ2 ሚሊየን 44 ሺህ 121 በላይ መሆናቸውን ጠቁመው÷ በቀሪ ቀናት ውስጥ የታቀደውን ለማሳካት እየተሠራ ነው ብለዋል።
በሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ 1 ሚሊየን 128 ሺህ 330 ዶዝ ክትባት በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ 30 ወረዳዎችና ሰባት የከተማ አስተዳደሮች እየተሰጠ መሆኑን ያነሱት ሃላፊው÷ በ3ኛው ዙር ሊሰጥ ከታሰበው የኮቪድ-19 ክትባት እስከ አሁን 92 በመቶ የህብረተሰብ ክፍል ማዳረስ ተችሏል ብለዋል፡፡
በክልሉ የሦስተኛው የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ በጤና ተቋማት፣ ሕዝብ በሚበዛባቸው ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች፣ በትምህርት ተቋማት እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ እየተሰጠ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.