Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ከተማ ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የፀጥታ አካላት በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ከተማ ያለውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታ አካላት በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ፡፡

የከተማውን ሰላም አስተማማኝ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በክልሉ ከሚገኙ የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በውይይት መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ማስቻል መሆኑን ገልጸው÷ ለዚህም ስኬታማነት በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታ አካላት የጋራ ትብብር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ሰሞኑን ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ በከተማዋ እየተስተዋለ ያለውን ስርዓት አልበኝነት ለመከላከልም የፀጥታ ኃይሉ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ከሰሞኑ ግጭት ጋር በተያያዘ የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው የፀጥታ አካላት እንዳሉ መንግስት ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በእነዚህ አካላት ላይም ተገቢውን ማጣራት በማከናወን ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ በዘላቂነት ሠላምን ማረጋገጥ እንደማይቻል ገልጸው÷ የከተማዋ ነዋሪዎች የፀጥታ ኃይሉ የሚፈልገውን መረጃ በመስጠት ለሰላሙ በአጋርነት እንዲቆሙ መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.