በአፋር ክልል ያለውን ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በክልሉ ያለውን ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡
የውይይት መድረኩ በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን÷ የክልል፣ የዞንና ወረዳ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
ምክክሩ በተለይም በክልሉ ያለውን ሰላም የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑም ተገልጿል።
የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም የሚያስችሉ ስራዎችን ለማከናወን የጋራ አቋም የሚያዝበትና ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት እንደሚሆንም የኢዜአ ዘገባ ይጠቁማል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!