Fana: At a Speed of Life!

ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ  አትሌቶች ሽኝት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኮሎምቢያ ካሊ በሚደረገው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶች ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተወካዮች በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል፡፡

በኮሎምቢያ ካሊ የሚደረገው ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ከነሃሴ 1 እስከ 6 ባሉት ጊዜያት የሚደረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.