Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘንድሮ 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር አተረፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ማትረፉን አስታወቀ።
ባንኩ የ2014 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት እያካሄደ ነው።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በግምገማው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፥ የባንኩ የካፒታል መጠን 59 ነጥብ 11 ቢሊየን ብር ደርሷል።
ባንኩ በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 824 ቅርንጫፎች እና 70 ሺህ ሠራተኞች እንዳሉትም ነው የተመለከተው።
ለአገሪቱ ኢኮኖሚ በተለይም ለግብርናው ዘርፍ ለማዳበሪያ ግዥ ብቻ ወደ 60 ቢሊየን ብር በማዋል የላቀ አስተዋፅኦ ማበርከቱም ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.