አሸባሪው ሸኔ መሽጎ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት የመደምሰስ እርምጃ እየተወሰደ ነው-የክፍለ ጦሩ ዘመቻ ኃላፊ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ሸኔ መሽጎ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት መደምሰስ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በስፍራው የተሰማራው የክፍለ ጦር ዘመቻ ኃላፊ ገለጹ፡፡
በቄለም ወለጋ ዞን በአሸባሪው ሸኔ ቡድን ላይ የማያደግም እርምጃ እየወሰደ ያለው ክፍለ ጦር የአሸባሪውን ቡድን ታጣቂዎች እግር በእግር እየተከታተለ መደምሰሱን ቀጥሏል ነው የተባለው።
የክፍለ ጦሩ ዘመቻ ኃላፊ ፥ በህዝባችን ደጀንንነት አሸባሪውን ሸኔ በማያዳግም ሁኔታ የምናጠፋበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ሲሉ ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም፥ አሸባሪው ሸኔ መሽጎ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች በጥናት በመለየት የመደምሰስ እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል።
የሬጅመንቱ ዘመቻ ኃላፊ በበኩላቸው፥ ሠራዊቱ ንፁሃንን ካለርህራሄ የሚጨፈጭፈውን ቡድን ለማጥፋት ትጥቁ ሳይላላ፣ ጉልበቱ ሳይዝል፣ በሞራል እና ወኔ በመንቀሳቀስ ጠላትን እየደመሰሰና ቁስለኛ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም፥ በየጫካው ስንቅና ትጥቅ ሲያጓጉዝባቸው የነበሩት የሞተር ሳይክሎችና የጋማ ከብቶችን በቁጥጥር ስር አውለናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!