የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ለ20 ጀኔራሎች ለእያንዳንዳቸው 150 ካ/ሜ ቦታ አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር የህልውና ዘመቻውን ከፊት እየመሩ ድል ላስመዘገቡ 20 ጀኔራሎች ለእያንዳንዳቸው 150 ካሬ ሜትር የቤት መስሪያ ቦታ አበርክቷል።
የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ መላሽ ወርቃለም÷ የአባቶቻችንን ታሪክ የደገሙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በህልውና ዘመቻው ከፊት ሁነው በመምራት ድል ማስመዝገባቸውን አውስተዋል፡፡
ጀግኖች ላደረጉት ተጋድሎ እና ላስመዘገቡት ድልም በከተማ አስተዳደሩ ሕዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ 20 ጀኔራሎች ለፈጸሙት ተጋድሎ ለእያንዳንዳቸው 150 ካሬ ሜትር የቤት መስሪያ ቦታ በስጦታ እንዳበረከተ መናገራቸውን ነው ከዋግ ኸምራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!