በእውቀት የታነጹ ሴቶችን ማፍራት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ተናገሩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእውቀትና በራስ መተማመን የታነጹ፣ ለሚቀጥለው የመሪነት እርከን ዝግጁ የሆኑ ሴቶችን ማፍራት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡
5ኛ ዙር ፕሬዚዳንታዊ የሴቶች የመሪነት ሥልጠና መርሐ ግብር 35 ሠልጣኞችን በማስመረቅ ተጠናቋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ÷ “በእውቀት፣ በክህሎትና በራስ መተማመን የታነጹ ለሚቀጥለው የመሪነት እርከን ዝግጁ የሆኑ ሴቶችን ማፍራት ቀዳሚ ጉዳይ ነው” ብለዋል።
ከጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን 143 በመካከለኛ የመሪነት እርከን ላይ ያሉ ከመንግሥት፣ ከሲቪል ማህበረሰብና ከግሉ ዘርፍ የተውጣጡ ሴቶች መሳተፋቸውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!