Fana: At a Speed of Life!

የታዳጊ ወጣቶች ውሃ ዋና ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ  ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን  አዘጋጅነት  ከነሀሴ 27 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የ2014 ዓ.ም  የታዳጊ ወጣቶች ውሃ ዋና ሻምፒዮና ተጠናቋል ።

 

በዚኅም የ2014 ዓ.ም የተደጊ ወጣቶች  የውሃ ዋና  ሻምፒዮና ከ14 ዓመት  በታች አዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር  በወንድ እና በሴት የዋንጫ ተሸላሚ  ሆኗል፡፡

 

ከ17 ዓመት በታች ምድብ በወንዶች ድሬዳዋ  አስተዳደር  የዋንጫ ተሸላሚ  በሴቶች  ደግሞ  የደቡብ ክልል አሸናፊ  በመሆን የዋንጫ  ሽልማት  አግኝተዋል ።

 

በሌላ በኩል ከ14 ዕድሜ በታች በወንዶች በፀሎት ሐፍቱ በ9 ወርቅ እንዲሁም በሴቶች ቅድስት ሙሉጌታ በ5 ወርቅ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮከብ  ስፖርተኞች  በመሆን ተመርጠዋል።

 

ከ17 ዕድሜ በታች ነቢዩ ኤልያስ ከቅዱስ ቂርቆስ ውሃ ዋና ስፖርት ክለብ 11 ወርቅ በማግኘት  ኮከብ  ሆኖ ሲመረጥ በሴቶች  ፌቨን አስናቀ  በ6 ወርቅ ኮከብ ተወዳዳሪ  በመሆን  ተመርጣለች ።

 

በሽልማት ሰነ ሰርዓቱ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር  ዴዔታ አምባሳደር  መስፍን  ቸርነትን ጨምሮ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት መሰረት ደምሱ  መገኘታቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.