ነገ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት በመዲናዋ ይሰጣል
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ ጳጉሜን 4 ነጻ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በመዲናዋ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ፥ “የአገልጋይነት ቀን” ን ምክንያት በማድረግ ነው የነጻ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹት፡፡
በዚህም አዳዲስ የሚሰማሩ አውቶቡሶችን ጨምሮ ፣ ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትና አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ በነፃ አገልግሎት እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡
አክለውም ፥ ጷጉሜን 4 “የአገልጋይነት ቀን” ብለን የሰየምነው ሁሉም ዜጋ የአገልጋይነት ባሕልን በማዳበር ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት እንድንችል ነው ብለዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ መጪው ዘመን የደስታ፣ የፍስሃ እና የስኬት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡