የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የእርድ ከብቶችን ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የእርድ ከብቶችን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሐቅ አብዱልቃድር እና የክልሉ ሰላም ግንባታ እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ በ22ኛ ክፍለ ጦር በመገኘት ለሠራዊቱ አስረክበዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር ÷የክልሉ መንግስት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የመከላያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
የ22ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ቡሽራ ሳኒ በበኩላቸው÷የክልሉ መንግስትና ሕዝብ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ ለሠራዊቱ የበለጠ ብርታት እንደሚሆን መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡