እስራዔል የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ያለውን አቋም አደነቀች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራዔል ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባዔ ዝቪ ሃውዘር የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ያለውን አቋም አደነቁ፡፡
በእስራዔል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ አለሙ ከእስራኤል ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባዔ ዝቪ ሃውዘር ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ረታ በዚህ ወቅት ፥ የኢትዮጵያ መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የወሰደውን እርምጃና አሸባሪው ህወሓት ውድቅ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
በዚህም አሸባሪው ቡድን ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት መክፈቱንም ነው የገለጹት፡፡
የእስራኤል መንግስት አሸባሪው ቡድን በኢትዮጵያ ላይ ያደረሰውን ጉዳት መጠን በመገንዘብ የኢትዮጵያን የሰላም ጥሪ እንደሚደግፍ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል አምባሳደሩ።
ምክትል አፈ ጉባዔ ሃውዘር በበኩላቸው ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላምን ለማስፈን እየወሰደ ያለውን አቋም እንደሚያደንቁ ገልጸዋል፡፡
መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ጸጥታን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያደንቁም ነው የተናገሩት፡፡
ምክትል አፈ ጉባዔው በአሸባሪው ቡድን የተጀመረውን ጦርነት በማውገዝ የመንግስትን የሰላም ጥሪ እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
ሀገራቱ ወዳጅነታቸውን በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ደረጃ ለማጠናከር መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!