Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፉ የፌዴሬሽን መድረክ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋዋን በአግባቡ ለመጠቀም እያከናወነች ያለውን ስራ አደነቀ

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የፌዴሬሽን መድረክ ፕሬዚዳንት ሩፓክ ቻቶፓዲያይ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋዋን በአግባቡ ለመጠቀም እያከናወነች ያለውን ስራ አድንቀዋል፡፡

 

ፕሬዚዳንቱ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ዘሀራ ኡመድ ፣ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና ከፌዴሬሽን መድረኩ የቦርድ አባል አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዲሁም ከሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን የእንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

 

በጉብኝታቸውም ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋ በሚገባ ለመጠቀም እያከናወነች ያለችውን በጎ ስራ አድንቀዋል።

 

መቀመጫውን ካናዳ ኦታዋ ያደረገው የፌዴሬሽን መድረክ በዓለም አቀፍ ዙሪያ በፌዴራል እና ያልተማከለ አስተዳደር አሠራር ላይ ተነፃፃሪ እውቀትን የሚያጎለብት እና የሚያጋራ ተቋም መሆኑ ተመላክቷል፡፡

 

የፌዴሬሽን መድረኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሕንድ፣ ጀርመን፣ብራዚል ፣ ናይጄሪያን እና ሌሎችንም ሀገራት በአባልነት ያቀፈ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.