Fana: At a Speed of Life!

ኢራን የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ መተማመኛ እንደምትፈልግ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ መተማመኛ እንደምትፈልግ አስታወቀች፡፡

የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የፈረንሳይ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ÷ ኢራን ተዓማኒ፣ አካታች እና ዘላቂ የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ ቁርጠኛ አቋም እንዳላት አብራርተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዘላቂ የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ተግዳሮት መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ለዚህ ደግሞ ተቋሙ በኢራን የኒውክሌር መርሐ ግብር ላይ ማጣራት እና ምርመራ ማድረግ አለብኝ የሚለው አቋሙ ስምምነት እንዳይደረስ ችግር መፍጠሩንም ነው ያነሱት።

ስለሆነም አስተማማኝ የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ ለአንድ ወገን የሚያደላው ዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በቴህራን ላይ ምርመራ ላድርግ የሚለውን ሃሳቡን ሊሰርዝ ይገባል ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቴህራን ከአውሮፓ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት መናገራቸውን ሺንዋ ዘግቧል፡፡

ይሁን እንጅ የግንኙነቱ መሻሻል አውሮፓውያን ከአሜሪካ ጥቅም ፣ ፍላጎት እና አመለካከት ነጻ መውጣት ላይ መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.