Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ችግር ለመቅረፍ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተስተዋለ ያለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ ያለመ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሽፈራው ተሊላ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክፍሌ ሆሮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ካሣሁን ከበደን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

አቶ አሻድሊ ሀሰን በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ የመተከልና ካማሺ ዞኖችን ጨምሮ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር አለ፡፡

ይህም የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆኑ ዘላቂ መፍትሔ ሊሠጠው እንደሚገባ በአጽንኦት መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ ያለውን የኤሌክትሪክ አቅርቦትና መቆራረጥ ችግር ለመፍታት ጊዜያዊና ዘላቂ የመፍትሔ እርምጃዎችን በመውሰድ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.