Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን እና ደቡብ ካሮላይና በ“ኢያን” አውሎ ነፋስ ተመቱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በዛሬው ዕለት የአሜሪካዎቹ ሰሜን እና ደቡብ ካሮላይና እጅግ አደገኛ በተባለለት የ “ኢያን”አውሎ ነፋስ እና ማዕበል ተመቱ፡፡

በፍሎሪዳ ሰሜን እና ደቡብ ካሮላይና አውሎ ነፋሱ ባስነሳው ማዕበል የ20 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ10 ቢሊየኖች ዶላር የሚቆጠር የንብረት ውድመትም መድረሱን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

በርካታ የባሕር ዳርቻ መዝናኛዎች እና ሆቴሎች መውደማቸውም ነው የተነገረው፡፡

በሳምንቱ የፍሎሪዳ የተለያዩ አካባቢዎች እና መንገዶች በጎርፍ ሲጥለቀለቁ መሰንበታቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል፡፡

በአውሎ ነፋስ እና በጎርፍ የወደቁ ዛፎች እና የኤሌክትሪክ ተሸካሚ ምሰሶዎች መንገድ ዘግተውም ነበር ተብሏል፡፡

ዛሬ በተመዘገበ መረጃ መሠረት በሰሜንና ደቡብ ካሮላይና እንዲሁም በፍሎሪዳ እስከ ጠዋቱ 2 ሠዓት ድረስ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን የሚጠጉ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ የኢያን አውሎ ነፋስ በደቡብ-ምሥራቅ የአሜሪካ ክፍል ባደረሰው ጉዳት ከ100 እስከ 120 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት እንዳስከተለም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በዛሬው ዕለት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰሜን ካሮላይና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውም ነው የተነገረው፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.