Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምስራቅ ሸዋ ዞን የበጋ መስኖ ስንዴ እየዘሩ ያሉ አርሶ አደሮችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ የበጋ መስኖ ስንዴ እየዘሩ ያሉ አርሶ አደሮችን ጎበኙ።

አርሶ አደሮቹ የመኸር ምርታቸውን አንስተው በትራክተር እያረሱ ይገኛሉ።

በዞኑ በበጋው 200 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ ይለማል።

እስከአሁን ባለው ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ታርሷል።

9 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በስንዴ መሸፈኑንም የዞኑ ግብር ጽህፈት ቤት ገልጿል ።

ኢትዮጵያ በዚህ አመት በበጋ በሁለት ዙር 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ ታለማለች።

ከዚህም 52 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ።

በአልዓዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.