Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት በታንዛኒያ በመንገደኞች አውሮፕላን በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መንግሥት የታንዛኒያ የመንገደኞች አውሮፕላን በቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ ተከስክሶ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ፡፡

በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ÷ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

49 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የታንዛኒያ የመንገደኞች አውሮፕላን በትናንትናው ዕለት ቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ መከስከሱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.