Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር ተወያይቷል፡፡
 
በአቶ አደም ፋራህ የተመራ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋን ያካተተው የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ በቆይታቸው ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ልዑኩ ከጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ አሕመድ የተላከን መልዕክት ለሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ማድረሱም ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.