በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃሙድ አሊ የሱፍ ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ በትኩረት መምከራቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ ባለፈም በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ነው የተገለጸው፡፡
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በትናንትናው ዕለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ መግባቱ ይታወቃል፡፡