በመብረቅ አደጋ የሁለት ታዳጊ ህፃናት ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በመብረቅ አደጋ የሁለት ታዳጊ ህፃናት ህይወት አለፈ፡፡
የከተማው ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን አዳነ አለማየሁ÷ በከተማው አዲስ ከተማ ቀበሌ ልዩ ስሙ ብርሃን አዲስ ከተማ ሠፈር ከቀኑ 8፡30 የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው መብረቅ የሁለት ህፃናት ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡
ሶስት ሆነው ውሃ ለመቅዳት ወንዝ በሄዱበት ወቅት ዝናብ በመዝነቡ ለመጠለል ዛፍ ስር በሚገኝ ድንጋይ ላይ በተቀመጡበት ወቅት በደረሰ የመብረቅ አደጋ ነው ሁለቱ ህፃናት ህይወታቸው ያለፈው፡፡
ለህልፈት የተዳረጉት የአምስት እና የሰባት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴትና ወንድ ህፃናት መሆናቸውን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡