Fana: At a Speed of Life!

ከቻይና አለም አቀፍ የንግድ ምክር ቤት ሃላፊዎችጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ ከቻይና አለም አቀፍ የንግድ ምክር ቤት ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ የኢንቨስትመንት  ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እና የቻይና አለም አቀፍ የንግድ ምክር ቤት ዳይሬክተር ጄኔራል ያንግ ሆንግ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን  ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የጋራ የንግድ እና የኢንቨስትመንት የማስተዋወቅ  ስራ በመስራት የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ከስምምነት መድረሳቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.