ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎበኝተዋል።
“ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ሃሳብ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተመርቆ ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉ ይታወቃል።
በአውደ ርዕዩ በግብርናው ዘርፍ የተለያዩ የምርምርና የፈጠራ ስራዎች፣ ዲጅታላይዜሽንና የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
አውደ ርዕዩን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየጎበኙት ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በስፍራው ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡
አቶ አወል አርባ በዚህ ወቅት÷ በአፋር ክልል የተሰሩ የግብርና ስራዎችን ለኤግዚቢሽኑ ማስረከባቸው ተጠቁሟል፡፡
በፈትያ አብደላ