በኢትዮጵያ የፈተና አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፈተና አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾን (ዶ/ር) ጨምሮ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ2015 ዓ.ም ክልላዊና ሀገራዊ ፈተና ማስፈጸሚያ ላይ ያተኮረ ውይይት በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ÷ በሀገራችን የፈተና አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
እንደሀገር በትምህርት ጥራት ውስጥ የሚታዩ ጉድለቶችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡
በዚህም በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡