Fana: At a Speed of Life!

ጂአይቴክስ አፍሪካ መድረክ  በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ  መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)  ጂአይቴክስ አፍሪካ 2023 መድረክ በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በአፍሪካ  ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው ጂአይቴክስ አፍሪካ  የኢትዮጵያ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

ለ 4 ቀን በሚቆየው ዝግጅት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትሩ  በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የተመራ የሚኒስቴሩ  የስራ ኃላፊዎች  እና የቴክኖሎጂ ጀማሪ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን በመወከል  እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘው ጂአይቴክስ አፍሪካ ዓላማው በአህጉሪቱ   እየተካሄደ የሚገኘውን የቴክኖሎጂ አብዮት ለተቀረው ዓለም ማስተዋወቅ ነው ተብሏል።

ዛሬ በተጀመረው የጂአይቴክስ አፍሪካ መድረክ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር)  እንደ አፍሪካ  በቅንጅት መካሄድ አለባቸው ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መስጠታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.