Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አምንቴ(ዶ/ር) በአፋር ክልል የእንስሳት መኖ ልማት ስራን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አምንቴ(ዶ/ር) በአፋር ክልል የእንስሳት መኖ ልማት ስራን በክልሉ ገቢ ረሱ ዞን ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ በክልሉ እየተከናወነ የሚገኘው እንስሳት መኖ ልማት በሀገር ደረጃ እየተከሰተ ያለውን የእንስሳት መኖ ልማት እጥረት እንደሚቀርፍ ገልፀዋል፡፡

የአፋር ክልል በእንስሳት መኖ ልማት ጥሩ ተሞክሮ እንዳለው የገለፁት ሚኒስትሩ ÷ የጉብኝቱ ዓላማ በእንስሳት መኖ ልማት ስራ  ውስጥ ድጋፍ  ለሚሹ  ወረዳዎች  የሜካናይዜሽን እገዛ ለማድረግ ያለመ መሆኑ አብራርተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ፥ አፋር ላይ የሚሰሩ ሰፋፊ የእንስሳት መኖ ልማት ስራዎች በሀገሪቱ የሚገኙ  አርብቶ አደሮችን ከችግር የሚያወጣ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከፍጆታ ባለፈ ኢትዮጵያ የእንሳሳት መኖን ወደ ውጭ እንድትልክ  የእንስሳት መኖ ስራ ላይ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.