Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አቀፉ የስደተኞች ፎረም ዝግጅት ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጭው ታህሳስ ወር ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ፎረም ዝግጅት ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።

አውደ ጥናቱን የኢፌዴሪ ስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት።

በተለይ ጦርነት ፣የምጣኔ ሀብት አለመረጋጋትና የጂኦፖለቲካ ተለዋዋጭነት ለፍልሰት ዋና ምክንያት መሆናቸው በአውደ ጥናቱ ላይ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ከጎረቤቶቿ በተለይም ከሶማሊያ፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን የተሰደዱ 1 ሚሊየን ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች ትገኛለችም ተብሏል።

በያዝነው አመት የካቲት ወር አንስቶ ብቻ ከሶማሊያ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተሰደዱ ከ100 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተነግሯል።

በአለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.