Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 2ኛው ምዕራፍ  የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ሁለተኛው ምዕራፍ  የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ  መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣  ከፍተኛ የፌዴራልና የከተማዋ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ አዲስ አበባን አረንጓዴ በማልበስ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ውብ ከተማ ለማድረግ ሁላችንም ችግኝ መትከል አለብን ብለዋል፡፡

ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ እንዲጸድቁ እና ፍሬ እንዲያፈሩ ማድረግ የሁሉም ነዋሪ ሃላፊነት እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሁለተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፍ አሻራቸውን እንዲያኖሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአዲስ አበባ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 17 ሚሊየን ችግኝ  ለተከላ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ከሚተከሉት ችግኞች መካከልም የተለያዩ የፍራፍሬ፣ለከተማዋ ውበት የሚሆኑ እና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የችግኝ አይነቶች ይገኙበታል ተብሏል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.