Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ሕዝቡ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ሕዝቡ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በንቃት እንዲሳተፍ የክልሉ ግብርና ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሻሚ አብዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በክልል ደረጃ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

ከሚተከሉት ችግኞች መካከልም 70 በመቶ የሚሆኑት የፍራፍሬ ሲሆኑ ÷ 30 በመቶዎቹ ደግሞ የደን ችግኞች ናቸው ብለዋል፡፡

የፊታችን ሐምሌ 10 ቀን ለሚከናወነው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 350 ሺህ ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ምክትል ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

በቀኑ የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸው ፍራፍሬዎችና የደን ዛፎች እንደሚተከሉ ጠቁመዋል።

መላው የሐረሪ ክልል ሕዝብም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.