Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል 18 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት ከ18 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱን የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ፈቃድ የተሰጠው በግብርና፣ አግልግሎት ሰጪ እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች መሆኑን የቢሮው ኃላፊ ሐልጌዮ ጂሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለ475 ፕሮጀክቶች ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ396 መሰጠቱን ጠቁመው÷ አፈጻጸሙም 83 ነጥብ 3 በመቶ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

አፈጻጸሙ ከቀደመው በጀት ዓመት አንጻር የ4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ብልጫ ማሳየቱንም ገልፀዋል።

ዘንድሮ ፈቃድ በተሰጠባቸው ፕሮጀክቶችም ለ9 ሺህ 652 ዜጎች ቋሚ እና ለ99 ሺህ 386 ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል።

በቋሚነት የተፈጠረው የሥራ ዕድል ከአለፈው ዓመት አንጻር የ11 በመቶ ቅናሽ፥ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል ደግሞ 25 በመቶ ብልጫ ያለው አፈጻጸም መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.