Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የሰው ኃይል ልማት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በታንዛንያ ዳሬሰላም ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው “የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት ማፋጠን፤ ወጣቶችን በትምህርት እና ክህሎቶች በማብቃት ምርታማነታቸውን ማሳደግ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ነው።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ በጉባኤው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በጉባኤው የአፍሪካ አገራት መሪዎችን ጨምሮ ከ30 አገራት የተውጣጡ ከ1 ሺህ 200 በላይ ተሳታፊዎች ታድመዋል።

የሰው ኃይል ልማት በኢኮኖሚ እድገት እና ዜጋ ተኮር ኢንቨስትመንት ላይ ያለውን ፋይዳ የተመለከቱ ጉዳዮች በጉባኤው ላይ ይመከርባቸዋል።

በጉባኤው የአፍሪካ አገራት የሰው ኃይል ልማት ስራዎች ተሞክሮ እንደሚቀርብ እና በዘርፉ ያሉ አዳዲስ እሳቤዎችን የተመለከቱ ሀሳቦች እንደሚሸራሸሩ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

ጉባኤው እስከ ነገ እንደሚቆይም ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.