በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ27 ነጥብ 1 ቢሊየን በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ27 ቢሊየን 187 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡
ፈቃድ የተሰጠው እርሻ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አገልግሎት፣ ሆቴልና ቱሪዝምን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች መሆኑ ተብራርቷል።
የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ከተማ ካሳ የዕቅዳቸውን 82 በመቶ መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
ለዕቅዱ ሙሉ በሙሉ አለመሳካትም በአንዳንድ አካባቢዎች የተስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች፣ በውሉ መሠረት በፍጥነት ወደ ሥራ አለመግባት እና ሌሎች ችግሮች በባለሃብቱ ዘንድ መስተዋሉን በምክንያትነት አቅርበዋል።
ፈቃድ በተሰጠባቸው ፕሮጀክቶች ከ7ሺህ 500 በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ነው አቶ ከተማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡
በክልሉ ለኢንቨስትመንት የሚውል 52 ሺህ ሄክታር መኖሩን እና ከዚህ ውስጥ 13 ሺህ ሄክታሩ ለአልሚዎች ለመተላለፍ ዝግጁ ስለመሆኑም አረጋግጠዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!