ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት አመት የደንበኞቹን ቁጥር 78 ሚሊየን ለማድረስ አቅዷል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት አመት የደንበኞቹን ቁጥር 78 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን አስታውቋል።
የቴሌብር ደንበኞች ቁጥሩንም ወደ 41 ነጥብ 1 ሚሊየን እንደሚያሳድግ ነው ያስታወቀው።
ኩባንያው የቀጣዩ አመት እቅዱን ይፋ አድርጓል።
ኩባንያው መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ተደራሽነቱን ለማሳደግ ማቀዱን ያስታወቀ ሲሆን÷ ገቢውን ለማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችንም እንደሚያስተዋውቅ ገልጿል።
የሞባይል ኔትዎርኮችን ማስፋፋት፣ የተቋማት አገልግሎት በቴክኖሎጂ ማገዝም በትኩረት እንደሚሰራበት ነው የተመላከተው።
ኢትዮ ቴሎኮም በመሰረታዊ የቴሌኮም አገልግሎት በአዳዲስ አገልግሎቶች በአጠቃላይ በመጪው አመት 90 ነጥብ 5 ቢሊየን ለማግኘት ማቀዱንም ገልጿል።
በትዕግስት ብርሃኔ