አቶ ሙስጠፌ ከዩኤስኤይድ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) የኢትዮጵያ ተወካይ እስኮት ሆክላደር ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በክልሉ መንግስት እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ መወያየታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በክልሉ የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ድጋፉ በአግባቡ እንዲደረስ ለማድረግ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውም ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!